ዜና አካባቢ ጥበቃ

ዜና አካባቢ ጥበቃ

ባለፉት ስድስት ወራት ከ58 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ከንክኪ ነጻ መደረጉን የአማራ ክልል አካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን አስታወቀ።
የአማራ ክልል ምክር ቤት የግብርና፣ አካባቢ ጥበቃ እና የውኃ ሃብት ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።
የባለሥልጣኑ ምክትል ኃላፊ አቶ በልስቲ ፈጠነ የአጣና ምርትን ከቦታ ቦታ ለሚያዘዋውሩ ግለሰቦች ፍቃድ በመስጠት ሃብቱ በሕጋዊ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል ነው ያሉት።
ባለፉት ስድስት ወራት ከ58 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ ከንክኪ ነጻ በማድረግ አካባቢው መልሶ እንዲያገግም እና ብዝኀ ሕይዎቱ መልሶ እንዲያንሰራራ መደረጉ በሪፖርቱ ቀርቧል።
በየአካባቢው የሚቋቋሙት ፕሮጀክቶች በአካባቢው ላይ ተጽዕኖ አለማሳደራቸውን እየተገመገሙ ነው ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ የሕግ ጥሰት በፈጸሙ 57 ፕሮጀክቶች ላይም አሥተዳደራዊ እና ሕጋዊ ርምጃ ተወስዷል።
ከኀብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ከፍተኛ የድምጽ ብክለት እየፈጠሩ የማኀበረሰቡን የቀን ከቀን ሕይዎት በሚያውኩ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይም እርምት ተሰጥቷል።
የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድን በተመለከተ ክትትል እና ድጋፍ መደረጉን ምክትል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በአካባቢ እና ደን ጥበቃ ዘርፍ ለተሰማሩ ከ55 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯልም ተብሏል። ባለፉት ስድስት ወራት ባለሥልጣኑ ከደን ውጤቶች 57 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ተጠቁሟል።

Related Posts

አካባቢ የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚወክለው የእንግሊዘኛ ቃል “ኢንቫይሮመንት” ፍቺው ኢንቫይሮነር (Environner)ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን ያጠቃለለ ማለት ነው፡፡ ይህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ

Learn More

proclamation no 1383 waste managment and desposal

Learn More

Related Videos

3 years ago

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *