የአካባቢ ፈቃድ፣ ምርመራና ቁጥጥር

የአካባቢ ፈቃድ፣ ምርመራና ቁጥጥር

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት (አብክመ) የአካባቢ፣ የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን (አደዱጥልባ) በክልል፣ በዞን፣ በወረዳና በጥብቅ ስፍራዎች ደረጃ የተዋቀረ ሲሆን በክልል ደረጃ ከሚተገበሩ ዋና ዋና የሥራ ሂደቶች አንዱ የአካባቢ ፈቃድ፣ ምርመራና ቁጥጥር ነው። ይህ ዋና የሥራ ሂደት የአካባቢ እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ማካሄድ ፣ ስልታዊ የአካባቢ ግምገማ ማካሄድ ፣ የአካባቢ ምርመራ ማድረግ ፣ የአካባቢ ክትትል እና ቁጥጥር ማካሄድ ፣ ለአካባቢያዊ አማካሪዎች የሙያ ፈቃድ መስጠትን እና ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያካተተ ነው፡፡

ከዚህ በታች በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአካባቢ ተጽዕኖ ምዘና መመሪያ (ቁጥር 001/2010) እና የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 181/2003) መሠረት የአስፈላጊ ቃላት መሰረታዊ ትርጓሜዎች ቀርበዋል፡፡

የአካባቢ እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ ምንድነው?

የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ማለት ኘሮጀክት፣ ፖሊሲ፣ እቅድ ወይም ፕሮግራም ተግባራዊ ሲሆን፣ ሲስፋፋና ሲቋረጥ በአካባቢ እና/ወይም በማህበራዊ ላይ የሚያስከትለውን ጠቃሚም ሆነ ጎጅ ዉጤትን ለይቶ የማወቂያና ለችግሮችም ማቃለያ ወይም ማስወገጃ ዘዴን የሚያመላክት ሂደት ነው፡፡

ተፅዕኖ ማለት በአካባቢ ወይም በንዑሳን ክፍሎች ላይ በሚፈጠር ለውጥ ምክንያት ማንኛውም በሰው ጤና ወይም ደህንነት፣ በዕፅዋት፣ በእንስሳት፣ በአፈር፣ በአየር፣ በውኃ፣ በአየር ንብረት፣በተፈጥሮአዊ ወይም በባሕላዊ ቅርስ፣ በሌላ ቁሳዊ አካል ወይም በአጠቃላይ ሲታይ በአካባቢያዊ፣ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ ወይም በባሕላዊ ገጽታዎች ላይ የሚከሰት ተከታይ ለውጥ ነው፡፡

የአካባቢ ምርመራ ማድረግ ስንል ምን ማለታችን ነው?

የአካባቢ ምርመራ ማለት አጠቃላይ የፕሮጀክቱን አፈፃፀም ከወጡ የአካባቢ ህጎችና ደረጃዎች ጋር ምን ያህል ተጣጥሞ እየሄደ እንደሆነ ለመገምገም፣ በአካባቢ ተጽዕኖ ጥናቱ የተለዩ ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ (ለማቃለል)፣ የታቀዱ ተግባራትን አፈፃፃምና ውጤታማነት ለማረጋገጥ፣ እየተተገበረ ያለው የአካባቢ አያያዝ እቅድ ያመጣውን ለውጥ ለመገምገም ወይም ፕሮጀክቱ ከአንዱ አካል ወደሌላ አካል ከመዛወሩ በፊት ያለውን አጠቃላይ የአካባቢ አያያዝ ሁኔታ ለማወቅ እንዲሁም ሊደርሱ የሚችሉ የአካባቢ ተጽዕኖዎችና አደጋዎችን ለመለየት እና ለችግሮቹ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል የአካባቢ መረጃን በተወሰነ የጊዜ ክፍተት የመሰብሰብ፣ የመለካት፣ ያሉ ሰነዶችንና ሪፖርቶችን የመመርመርና የመተንተንን ሂደቶች ያካትታል፡፡

የአካባቢ ክትትል እና ቁጥጥር ምንድነው?

የአካባቢ ክትትል ማለት በአካባቢ ተጽዕኖ ጥናት ሪፖርት ውስጥ በአካባቢ አያያዝ ዕቅድ ላይ የታቀዱ የማቅለያ ተግባራት ስለመፈፃመቸው፣ ከተተነበዩ ተጽዕኖዎች በተጨማሪ ሌሎች አዳዲስ ተፅዕኖዎች ስለመከሰታቸው፣ በመሰረታዊ የአካባቢ መረጃ ላይ የተለዩ የአካባቢ ጉዳዮች በትግበራ ጊዜ ምን ያህል እንደተለወጡ፣ የፕሮጀክት ትግበራ ከወጡ የአካባቢ ህጎች ጋር ምን ያህል ተጣጥሞ እየተተገበረ እንደሆነና የማቅለያ ተግበራት አፈጻጸም ውጤታማነትን ለመገምገምና ወቅቱን የጠበቀ የማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ስልታዊና ተከታታይነት ያለው መረጃን የመሰብሰብ፣ የመለካት፣ የመተንተንና የማስተካከያ እርምጃ የመውሰድ እና የመደገፍ ሂደት ነው፡፡

የአካባቢ ቁጥጥር (Inspection) ማለት ጥርጣሬ ሲኖር ወይም ጥቆማ ሲደርስ የሚካሄድ ድንገተኛ የአካባቢ ፍተሻ ወይም ቀደም ሲል በተካሄደ የአካባቢ ክትትልና ምርመራ ላይ የተሰጠ ግብረመልስን የአፈፃፀም ደረጃ ለማረጋገጥ ወቅቱን ባልጠበቀ ምልከታ የምናረጋግጥበትና በቁጥጥሩም መሰረት የተለያዩ ህጋዊና አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃዎችን የምንወስንበት ሂደት ነው፡፡

የይሁንታ ፈቃድ ስንል ምን ማለታችን ነው?

የይሁንታ ፈቃድ ማለት ማንኛውም ሰው ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት ለቢሮዉ ወይም ለሚወክለው አካል የሚያቀርበው ፕሮጀክት ወይም ሰነድ ወይም ፕሮግራም ወደ ሥራ ቢገባ የጎላ ችግር የሌለበት መሆኑን በአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ መመዘኛ መሠረት ተረጋግጦ ሥራውን እንዲሠራ የሚሰጥ ፈቃድ ነው፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአካባቢ እና ማህበራዊ ተጽዕኖ ግምገማ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 181/2003 ዓ.ም) እና የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ መመሪያ (ቁጥር 001/2010) ይመልከቱ፡፡

Related Posts

አካባቢ የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚወክለው የእንግሊዘኛ ቃል “ኢንቫይሮመንት” ፍቺው ኢንቫይሮነር (Environner)ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን ያጠቃለለ ማለት ነው፡፡ ይህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ

ተጨማሪ እወቅ
የአካባቢ፣ የደንና የዱር እንስሳት አያያዝ ጥናት

የአካባቢ፣ የደንና የዱር እንስሳት አያያዝ ጥናት

ተጨማሪ እወቅ

የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ መመሪያ

Final ESIA Directives, Nov (2018

ተጨማሪ እወቅ

Related Videos

3 years ago

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *