በዳይሬክቶሬት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
- የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት
- የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና ወቅታዊ መረጃ ማድረስ
- የምክክር አውደ ጥናት ማካሄድ፤
- በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩና ግንዛቤን ማጎልበት የሚያስችሉ የሬዲዮ/ቴሌቪዥን ዶክመንታሪዎች ለህዝብ ማድረስ፤
- በኤግዚቢሽኖች፣ ሀይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት እንዲሁም በስብሰባ ቦታዎች ላይ በመገኘት ለህ/ሰቡ ወቅታዊ መረጃ መስጠት፤
- ከመገናኛ ድርጅቶች የአየር ስዓት በመግዛት ወይም በትብብር በማግኘት ለህብረተሰቡ መረጃ መስጠት፤
- በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ህትመቶችን በማሳተምና በማሰራጨት ለህ/ሰቡ መረጃ ተደራሽ ማድረግ፤
- የአካባቢ እንክብካቤ ክበባትን በት/ቤት ማጠናከርና መደገፍ፤
- የአካባቢ እንክብካቤ ክበባትና ተቆርቋሪ ማህበራትን ከት/ቤት ውጭ ማደራጀትና ማጠናከር
- የዓለም የአካባቢ ቀን እና የበረሃማነት ቀን በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ማክበርና የህዝብ ንቅናቄ መፍጠር
- ቸክሊስ በማዘጋጅት ድጋፍና ክትትል ማካሄድ