የህብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግና የመረጃ ተደራሽነት

የህብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግና የመረጃ ተደራሽነት

የአካባቢ ፣ የደን እና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ዋና የሥራ ሂደቶች መካከል የህብረተሰቡ ግንዛቤ ማሳደግ እና የመረጃ ተደራሽነት አንዱ ሂደት ሲሆን የሚተገበረውም በተመሳሳይ ስም በሚታወቀው ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአካባቢ፣ የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን በ2008 ዓ.ም ከተቋቋመ በኋላ በዚያው ዓመት በዋና ዋና የሥራ ሂደቶች ላይ ማሻሻያ አድርጓል። ከዋና ዋናዎቹ የሥራ ሂደቶች አንዱ የህብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግና የመረጃ ተደራሽነት ነው፡፡ በባለሥልጣኑ ውስጥ የህብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግና የመረጃ ተደራሽነት ዋና ሥራ ሂደትን ለማዋቀር በተዘጋጀው የአሠራር ማሻሻያ ጥናት ሰነድ ውስጥ የሚከተሉት ነጥቦች እንደ አስፈላጊ ምክንያቶች ተገልጸዋል፡፡

  • ባለስልጣኑ አዲስ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር ለማስፈጸም እና በክልሉ የተሻለ የህብረተሰብ ግንዛቤ ለመፍጠርና ተደራሽነት ያለው መረጃ ለመስጠት የሚያስችል አደረጃጀት ከክልል እስከ ወረዳና ጥብቅ ስፍራ ለመዘርጋት ሰነዱን እንደገና ማሻሻል በማስፈለጉ፤
  • አካባቢ ጥበቃ ከሰብዓዊ መብት መጠበቅ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው በመሆኑ በክልሉ ያሉ ቁልፍ የአካባቢ የእውቀትና ክህሎት ክፍተቶችን በመለየት ለህብረተሰቡ ወቅታዊ መረጃና ግንዛቤ በመስጠት የክልሉን ህብረተሰብ የአካባቢ መብቶቹን እንዲያስጠበቅ አቅሙን ማጎልበት በማስፈለጉ፤
  • በብዝሃ ህይወት፣ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብቶች አያያዝና አጠቃቀም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ከተለመደው አሰራር በተሻለ መስራት በማስፈለጉ፤
  • ህብረተሰቡ በእውቀት፣ በአስተሳሰብ፣ በአመለካከት፣ በክህሎትና በተሳታፊነት ላይ ያተኮረ አካባቢን፣ ደንና ዱር እንስሳትን በማልማት፣ በመንከባከብና በመጠቀም ለዘላቂ ልማትና ዕድገት እንዲተጋ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤
  • እና ሌሎችም ናቸው፡፡

በዚህም መሠረት የባለስልጣኑን አዲሱን አደረጃጀት ተከትሎ በተለያዩ መ/ቤቶች ሲሰጥ የነበረውን የትምሀርት፣ ግንዛቤና መረጃ አያያዝ ተግባራትን ወደ አንድ በማምጣት የአሰራርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመለየት ሕብረተሰቡን በይበልጥም ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ቀልጣፋና ውጤታማ የስራ ሂደት አስፈላጊ ስለሆነ የህብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግና የመረጃ ተደራሽነት ዋና የስራ ሂደት በአዲስ እንዲደራጅ ተደርጓል።

ይህ ተሻሻሎ በአዲስ የተቋቋመው የስራ ሂደት ቀደም ሲል በተለያዩ መ/ቤቶች ሲካሄዱ የነበሩ ተግባራትን ወደ አንድ ማዕከል እንዲመጡ በማድረግ የደንበኞችን ፍላጎት፣ ጥያቄና ችግሮች በሚመልስ መልኩ ግብዓትን በማስቀደም እስከ ውጤት በሚያደርስ ሁኔታ ተደራጅቷል።

 

Related Posts

አካባቢ የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚወክለው የእንግሊዘኛ ቃል “ኢንቫይሮመንት” ፍቺው ኢንቫይሮነር (Environner)ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን ያጠቃለለ ማለት ነው፡፡ ይህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ

ተጨማሪ እወቅ

Best Practice

gordema Club Best practices best practice

ተጨማሪ እወቅ

አካባቢ ምን ማለት ነው?

አካባቢ የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚወክለው የእንግሊዘኛ ቃል “ኢንቫይሮመንት” ፍቺው ኢንቫይሮነር (Environner)ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን ያጠቃለለ ማለት ነው፡፡ ይህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ

ተጨማሪ እወቅ

Related Videos

3 years ago

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *