አካባቢ ምን ማለት ነው?

አካባቢ የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚወክለው የእንግሊዘኛ ቃል “ኢንቫይሮመንት” ፍቺው ኢንቫይሮነር (Environner)ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን ያጠቃለለ ማለት ነው፡፡ ይህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ ያሉትን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን እንደ አፈር፣ ውኃ፣ አየር፣ የሰው ልጅ፣ እፅዋት፣ እንስሳት፣ አነስተኛ ነፍሳትና ሌሎችንም ሁሉ ያጠቃልላል፡፡ ቀስ በቀስም አካባቢ ለሚለው ቃል ሰፊ ትርጉም በመስጠት ሰዎችን ጨምሮ ሌሎች ሕይዎት ያላቸው ነገሮች ከቁሳዊው ዓለም ጋር ያላቸው ተራክቦ ወይም ግንኙነት እንዲጨምር ተደረገ፡፡ ከዚያም ሁኔታዎች እየተሻሻሉና ዕድገት እየተፋጠነ ሲሄድ ፍቺው ወይም ትርጉሙም በዚያው ልክ እየሰፋ የሰው ልጅ በሚያደርጋቸው የማህበራዊ፣ ባህላዊና የቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎች ከአካባቢ ጋር ቁርኝት እንዳላቸው በማረጋገጥ እነዚህን ሁሉ ጉዳዮች እንዲያካትት ተደርጓል፡፡ በዚህም ምክንያት የሰው ልጅ የሚገነባቸው ግንባታዎች፣ ቁሳቁስ፣ እናቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ሁሉ በዚህ ትርጉም ውስጥ ተካትተዋል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ አካባቢ የሚለው ቃል ሕይዎት ያላቸውን እና ሕይዎት የሌላቸውን ነገሮች ሁሉ የሚያጠቃልል ሆኗል፡፡ የኢኮኖሚና ቴክኖሎጂ ልማት ዕድገት በማህበረሰቡ የማህበራዊና ባህላዊ ሁኔታዎች ላይ ተፅዕኖስለሚያሳድር አካባቢ የሚለው ቃል ሰፋ ያለ እይታ እንዲኖረው በማድረግ ማናቸውንም በዓለማችን ያሉ ነገሮችንና በመካከላቸው ያለውን ተራክቦ ወይም ግንኙነት ሁሉ ይዟል፡፡

Related Posts

አካባቢ የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚወክለው የእንግሊዘኛ ቃል “ኢንቫይሮመንት” ፍቺው ኢንቫይሮነር (Environner)ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን ያጠቃለለ ማለት ነው፡፡ ይህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ

ተጨማሪ እወቅ
የህብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግና የመረጃ ተደራሽነት

የህብረተሰብ ግንዛቤ ማሳደግና የመረጃ ተደራሽነት

የአካባቢ ፣ የደን እና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ዋና የሥራ ሂደቶች መካከል የህብረተሰቡ ግንዛቤ ማሳደግ እና የመረጃ ተደራሽነት አንዱ ሂደት ሲሆን የሚተገበረውም በተመሳሳይ ስም

ተጨማሪ እወቅ

Best Practice

gordema Club Best practices best practice

ተጨማሪ እወቅ

Related Videos

3 years ago

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *