የዱር እንስሳት ጥበቃ እና ልማት

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን በተቋም ደረጃ በ1956 ዓ.ም የደንና የዱ,ር አራዊት ድርጅት ተብሎ በእርሻ መኒስቴር ስር ተቋቋመ፡፡ በ1972 ዓ.ም ስያሜዉን ቀይሮ የዱር እንስሳት ጥበቃ ድርጅት ተብሎ በግብርና መኒስቴር ስር በመምሪያ ደረጃ ተደራጅ፡፡ በ2000 ዓ.ም በፌደራል ደረጃ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሰልጣን ተቋቁሞ አስራ ሶስት የዱር እንስሳት ጥበቃ ስፍራዎችን እያስተዳደረ ይገኛል፡፡

በአማራ ክልል በርካታ የዱር እንስሳትና ማራኪ የተፈጥሮ መኖሪያ አካባቢዎች ቢኖሩም በ1961 ዓ.ም ከተቋቋመዉ የስሜን ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክና በ1970 ዓ.ም በዩኔስኮ የአለም የተፈጥሮ ቅርስነት ተመዝግቦ፤ በ1988 ዓ.ም የብዝሃ ህይዎት ሃብቱ በመቀነሱና ብሄራዊ ፓርኩ በመጎሳቆሉ በዩኔስኮ የአደጋ መዝገብ ተመዝግቦ የነበረዉና በ2008 ዓ.ም በማገገሙ ከዩኔስኮ አደጋ መዝገብ ከተሰረዘዉ የስሜን ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ በስተቀር ከ1996 ዓ.ም በፊት ሌላ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘ የዱር እንስሳት ጥበቃ ስፍራና በክልለ ደረጃ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ተቋም አልነበረም፡፡

በ1988 ዓ.ም የስሜን ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ በዩኔስኮ አደጋ መዝገብ መመዝገቡን ተከትሎ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ በሰጠዉ ትኩረት በ1996 ዓ.ም የአብክመ ፓርኮች ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን በአብክመ ምክር ቤት በዝክር ህግ ደንብ ቁጥር 96/1996 ተቋቋመ፡፡

በመቀጠልም በ2001 ዓ.ም የስሜን ተራራዎችና የአልጣሽ ብሄራዊ ፓርኮች በፌደራል የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን እንዲተዳደሩ መደረጋቸዉን ተከትሎ የአብክመ ፓርኮች ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የነበረዉ በአብክመ ባህል ቱሪዝምና ፓርኮች ልማት ቢሮ በዱር እንስሳት ጥናት፤ ልማትና አጠቃቀም ዋና የስራሂደት ተደራጀ፡፡

ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ አካባቢ ጥበቃ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ባለስልጣን በሁለት በመከፈል የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ራሱን ሲችል የአካበቢ ጥበቃ ዘርፈፍ የደን እንክብካቤና የዱር እንስሳቱን ልማትና ጥበቃ እንዲያስተዳድር ተጨማሪ ሃላፊነት በመስጠት በአብክመ ዝክረ ህግ በደንብ ቁጥር 232/2008 በአብክመ አካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ዳሬክቶሬት ተብሎ ቀደም ሲል በባለስልጣን ደረጃ የተሰጡትን ሃላፊነቶች እንደያዘ በባለስልጣኑ ስር ሆኖ የክልሉን የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡