የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ዳራክቶሬት ተግባርና ሃለፊነት

የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ዳራክቶሬት ተግባርና ሃለፊነት

ሀ) በክልሉ በተቋቋሙና በሚቋቋሙ ብሄራዊ ፓርኮችና ሌሎች የዱር እንስሳት ጥበቃ ስፍራዎችን ያጠናል፤ ይከልላል፤ ህገዊ ሰዉነት ያሰጣል፤ ይመዘግባል ያስተዳድራል፡፡

ለ) የክልሉን ስርዓተምህዳር ወይም ኢኮሲሲተም በሚወክሉ የተለያዩ ስፍራዎች የዱር እንስሳት፤ አእዋፋትና አጽዋት ቦታዎችና ፓርኮች እንዲቋቋሙና ኢትዮጵያ በፈረመቻቸዉ አለማቀፍ ስምምነቶች /ፕሮቶኮሎች/ መሰረት እንዲለሙና ለትዉልድ እንዲተላለፉ ያደርጋል፡፡

ሐ) ብርቅየና ቁጥራቸዉ ተመናምኖ በመጥፋት ስጋት ላይ ላሉ የዱር እንስሳት ዝርያዎች ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ ያደርጋል፡፡

መ) የክልሉ ህብረተሰብ በዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ረገድ እንዲሁም በትክክለኛ የአጠቃቀም ስርዓት ላይ በቂ ግንዛቤ ሊያገኘ የሚችልበትን ስልት ቀይሶ በስራ ላይ ያዉላል፡፡ የመሬት አጠቃቀም ከጥበቃዉ አላማ ጋር የሚተሳሰርበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

ሠ) በብህራዊ ፓርክችና በሌሎች የዱር እንስሳት መጠለያ በተከለሉ ጥበቃ ስፍራዎች የሰፈረዉ ነዋሪ ህዝብ ወደ ሌላ አካባቢ የሚዛወርበትን ስልት ህብረተሰቡ ራሱ በተሳተፈበትና የመፍትሄዉ አካል ሁኖ በሚቀርብበት አኳኋን ይቀይሳል፡፡

ረ) በብሄራዊ ፓርኮችና ሌሎች የዱር እንስሳት መኖሪያ አካባቢዎች ዉስጥ የተፈጥሮ ዉበት ወዳላቸዉ ቦታዎች የሚያመላልሱ የቱሪስት ጉዞ መስመሮችና መመልከቻ ቦታዎች እንዲሰሩና እንዲደራጁ ያደርጋል፡፡

ሰ) ለቱሪስቶች አገልግሎት የሚሰጡ ካምፖች፤ ሎጆች ማረፊያዎችና የመሳሳሉት ከሚሰሩበት የተፈጥሮ አካባቢዎች ጋር በማይጋጭ አኳኋን ሊገነቡ የሚችልበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡ በህብረተሰቡና በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ተሳትፎ እንዲሰሩ ያደርጋል፡፡

ሸ) በዉጫዊይም ሆነ ዉስጣዊ ምክንያት በዱር እንስሳትና በመኖሪያ አካባቢያቸዉ ሊደርስባቸዉ የሚችለዉን በሽታና ሌሎች አደጋዎችን ለመከላካል፤ ለመቆጣጠርና ለማጥፋት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊዉን ይፈጽማል፡፡

ቀ) የዱር እንስሳትን የፓርኮችንና የጥብቅ ስፍራዎችን ልማትና አጠቃቀም የሚመለከቱ ደንቦችንና መመሪያዎችን ያዘጋጃል ሲፈቀድለትም በስራ ላይ ያዉላል፡፡

በ) የዱር እንስሳት እርባታና ማሳያ ቦታዎችን ለማቋቋም የሚፈልጉ ባለሃብቶች ጥያቄ ሲቀርብለት የሙያ ድጋፍ ይሰጣል፡፡

ተ) የዱር እንስሳት፤ አእዋፋት፤ ቀጣይ ህልዉናቸዉን በማይጋፋ መንገድ ለቱሪዝም፤ ለአደን፤ ለህይወት ንግድና ለእርባታ ሊዉሉ የሚችሉባቸዉን ደንቦች ያዛጋጃል፤ ሲጸድቅም በተግባር ላይ ያዉላል፡፡

ቸ) በዱር እንስሳትና በዱር እንስሳት ዉጤቶች ንግድ ለሚሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች፤ በንግዱ የመሳተፍ ብቃታቸዉን ገምግሞ ማራጋገጫ ይሰጣል፡ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡

ነ) በንግድ ስራ ወይም በሌላ በማናቸዉም ምክንያት ከቦታ ወደ ቦታ ለሚንቀሳቀሱ የዱር እንስሳትና የዱር እንስሳት ዉጤቶች መነሻና መድረሻቸዉን የሚያመላክት የምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡

ኘ) ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት በፓርኮችና በሌሎች ጥብቅ ሰፍራዎች አካባቢ የሚገኘዉን ህብረተሰብ ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ከጥበቃዉ ጋር ተስማሚና ዘላቂ የሆኑ አማራጭ የገቢ ምንጮችን እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡ በተመሳሳይ ለፓርኮችና ሌሎች ጥብቅ ሰፍራዎች ልማት ምቹ የሆኑ የቱሪዝም አይነቶችን ይለያል፤ ያስተዋዉቃል፡፡

ኸ) ስለዱር እንስሳት እንዲሁም ስለመኖሪያ ስፍራወቻቸዉ ሳይንሳዊ ምርምር ያደርጋል፡፡ በሌሎችም ሊካሄድ የሚችልበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤ የጥናት ዉጤቶቹም ስራ ላይ ያዉላል፡፡

ኀ) በህገዎጥ መንገድ ሲዘዋወሩም ሆነ በግለሰቦችና ህገዊ ባልሆኑ አካላት ተይዘዉ የሚገኙ የዱር እንስሳትና ዉጤቶቻቸዉን በቁጥጥር ስር ያዉላል፡፡ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ ለህግ ቀርባል፤ ዉሳኔ የተሰጣቸዉን የዱር እንስሳት ዉጤትና ለዚሁ ስራ ላይ የዋለ የጦር መሳራያ፤ ወይም ሌላ መገልገያ ይረከባል፤ እንዳስፈላጊነቱ፤ ለጥናት ለሙዚየም፤ ለቱሪዝም፤ ለትምህርት አገልግሎት ለሌላ አካል ያስተላልፋል፡፡ ጥቅም ላይ የማይዉለዉን ያስወግዳል፡፡

Related Posts

አካባቢ የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚወክለው የእንግሊዘኛ ቃል “ኢንቫይሮመንት” ፍቺው ኢንቫይሮነር (Environner)ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን ያጠቃለለ ማለት ነው፡፡ ይህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ

ተጨማሪ እወቅ
የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ የትኩረት መስኮች

የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ የትኩረት መስኮች

የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ስትራቴጅያዊ የትኩረት መስኮች፡– የዱር እንስሳትና መኖሪያ አካባቢያቸዉን ጥበቃና ልማት ቀጣይነት ማረጋገጥ የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች የሳይንሳዊ ምርምርና የትምህርት ማዕከልና ህያዉ ቤተሙከራ

ተጨማሪ እወቅ
የዱር እንስሳት ሀብት ልማትና ጥበቃ

የዱር እንስሳት ሀብት ልማትና ጥበቃ

በአማራ ክልል የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ሥራዎች የሚተገበሩትና የሚተዳደሩት በኢፌዲሪ የዱር እንስሳት ልማት ፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 544/1999 ፤ እንዲሁም የዱር እንስሳት ልማት ፣

ተጨማሪ እወቅ
የዱር እንስሳት ጥበቃ፣ ልማትና አጠቃቀም

የዱር እንስሳት ጥበቃ፣ ልማትና አጠቃቀም

ተጨማሪ እወቅ

Related Videos

3 years ago

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *