የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት

የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት

አካባቢ ለሰው ልጅ የሚያስፈልጉ ቁሳዊና ስነ–ልቦናዊ ፍላጐቶች ምንጭ ነው፡፡ እነዚህ ፍላጐቶች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ይሳኩ ዘንድ ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡ አካባቢ ከምንተነፍሰው አየር ጀምሮ የምንጠጣው ውሃ፣ የምንመገበው ምግብ ምንጭነት በተጨማሪ የሰው ልጅ በመኖር ሂደት የሚፈጥራቸውን ቆሻሻዎች በመሸከምና በማምከን ተኪ የሌለው ሚና ይጫወታል፡፡

የአካባቢ የቁስ አቅርቦትና ቁሳዊ ያልሆኑ አገልግሎቶችን ዘላቂ በሆነ ሁኔታ መስጠት እንዲችልና የተፈጥሮ ሀብቱ ለትውልድ እንዲተላለፍ የሰው ልጅ መስራት ያለበትን ስራ ባለመስራቱ አካባቢያችን ለከፍተኛ ጉስቁልና ተዳርጓል፡፡ የአካባቢ አየር ሙቀት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ በየአመቱ እጅግ ብዙ የብዝሃ ህይወት ሃብት ከምድር በመጥፋት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የምድር ገፅ መቆሳቆል ፣ አፈር መሸርሸር፣ የውሃ አዘል መሬቶች መመናመን፣ የተፈጥሮ ደኖች መመንጠርና መጐሳቆል፣ የአካባቢ ብክለት፣ የተፈጥሮ ሀብት ብክነት አሁናዊ ክስተት ሁነዋል፡፡

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ስርጭት፣ አደጋ የሚያስከትል ተለዋዋጭ የሆኑ ክስትቶች መበራከት፣ ከዚህ በፊት ታይተው የማይታወቁ ወራሪ አረሞችና ነፍሳት መበራከት፣ አዳዲስ የበሽታ ክስተቶች፣ የሚጠበቁ ውጤቶች መሆናቸው አይቀርም፡፡

በመሆኑም የሰው ልጅን ህይወት ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሰውና አካባቢ ተጣምረው እንዲሄዱ ማድረግ ይቻል ዘንድ የአካባቢ ጥበቃን ጉዳይ ታሳቢ ተደርጐ መሄድ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን መዘዙ እንዲህ በቀለሉ የሚገመት አይደለም፡፡

አገራችን ኢትዮጵያም ይህንን ታሳቢ በማድረግ በርካታ አለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ስምምነቶችን የፈረመች አገር ስትሆን የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ የተካተተበት ህገመንግስትም አርቅቃለች፡፡ በዚህ ህገመንግስት ጉልህ ሆኖ ከወጣው ጭብጥ ሃሳብ ውስጥ ዜጐች ባልተበከለና ንፁህ በሆነ አካባቢ የመኖር ዋስትና ያላቸው መሆኑ የተመላከተበት ነው፡፡

የህገመንግስቱን የአካባቢ ጥበቃ ጭብጥ ታሳቢ በማድረግ አገራችን ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ፖሊሲን በ1989 ዓ/ም ያረቀቀችና ወደ ስራ ያስገባች ሲሆን ይህንን ተከትሎ በርካታ ህጐችና ደንቦች የወጡ ሲሆን የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር አዋጅ 300/1995 እና የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አዋጅ 299/1995 ሣይጠቀሱ አይታለፉም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ በ2011 እ.ኤ.አ. ያፀደቀችው ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጅ ሣይጠቀስ አይታለፍም፡፡

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም የፌደራሉን አዋጅ በመከተል የራሱን የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ አዋጅ 183/2001 በስራ ላይ ያዋለ ሲሆን የአካባቢ ጥበቃን ጉዳይ እራሱን ችሎ የሚመራ ተቋም በአዋጅ ቁጥር 232/2008 የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን አቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

ባለስልጣኑ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸውን የስራ ዘርፎች ለመጥቀስ ያክል በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ጥብቅ ደኖችን መጠበቅና መንከባከብ በክልሉ ውስጥ የሚገኙና ከ10 በላይ የሆኑ የማህበረስብ ጥብቅ ስፍራና ብሄራዊ ፓርኮችን ማስተዳደር እንዲሁም በክልሉ የሚካሄዱ አገልግሎት ሰጪና የልማት ፕሮጀክቶች ከአካባቢ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን የማረጋገጥ፣ የመከታተል፣ የመቆጣጠርና ኦዲት የማድረግ ስራ እንዲሁም ለአየር ንብረት የማይበገር ኢኮኖሚ ስትራቴጅን በክልሉ የማስተባበር ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ አደረጃጀቱንም በዞንና በወረዳ ደረጃ በማጠናከር ላይ ይገኛል፡፡

ባለስልጣን መ/ቤቱ በአሁኑ ወቅት በርካታ ከአካባቢ ጥበቃና ደን ልማት ጋር የተያያዙ ፕሮጀክቶችን በማስተባበር ላይ ሲሆን በየጊዜው ተቋማዊ አቅሙን በማሳደግ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ የሁሉንም ዜጐች ተሳትፎ የማጠይቅ በመሆኑ በምናደርገው ሁሉን አቀፍ እርብርብ ከተቋማችን ጐን እንድትቆሙ እናሳስባለን፡፡

በላይነህ አየለ (ፒ ኤችዲ)

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ተባባሪ ፕሮፌሰር
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የአካባቢ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር

ኢሚል: belaynehayele@efwpdaamhara.net, belaynehayele47@gmail.com

Related Posts

አካባቢ የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚወክለው የእንግሊዘኛ ቃል “ኢንቫይሮመንት” ፍቺው ኢንቫይሮነር (Environner)ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን ያጠቃለለ ማለት ነው፡፡ ይህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ

ተጨማሪ እወቅ

እሴቶች

የአካባቢ ደህንነትና ዘላቂነትን ማረጋገጥ፣ የህብረተሰብ ተጠቃሚነት፣ የብዝሀ ህይዎት ሃብትን መንከባከብ፣ ለለውጥ ዝግጁነት፣ የሙያ ፍቅር፣ ታታሪነትና ውጤታማነት፣ የላቀ አገልግሎት፣ አሳታፊነት፣ የህግ የበላይነት

ተጨማሪ እወቅ

የእኛ ራዕይ

የእኛ ራዕይ: የአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነትን በማረጋገጥ፣ የደንና የዱር እንስሳት ሃብትን በአግባቡ በመጠበቅና በማልማት፣ በ2017 ለሰውና ለዱር እንስሳት መኖሪያ ምቹ የሆነ አካባቢ ተፈጥሮ ማየት፤

ተጨማሪ እወቅ
ተልእኳችን

ተልእኳችን

በሳይንሳዊ እውቀት ላይ ተመስርቶ በክልሉ አካባቢን የሚጎዱና የሚበክሉ ተግባራትን በመከታተል፣ በመመርመርና በመቆጣጠር፣ የብዝሃ ህይዎት ሃብት መመናመንን በመከላከል የቀጣዩን ትውልድ የመወሠንና የመጠቀም መብት ሣይጋፋ በዘመኑ ላለው

ተጨማሪ እወቅ

Related Videos

3 years ago

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *