ዋናዋና ተግባራት
- የአካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት አያያዝ ጥናት ማካሄድ
- ህብረተሰቡን ያሳተፈ የጥብቅ ቦታዎች ልየታና ክለላ ማካሄድ
- የአካባቢ ሀብቶች ዋጋ ትመና
- የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን ተግባራዊነት ማሳለጥና ለቴክኖሎጅ ሽግግር ድጋፍ ማድረግ
ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ መገንባት
ለአየር ንብረት አለመበገር ማለት በአየር ጠባይ ጫናዎችና በሚከሰቱት ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት የሚመጡ ለውጦችን የመቋቋምና ችግሮቹንም የመግታት ችሎታ ማበጀት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ለአየር ንብረት የማይበገር ኢኮኖሚ በአየር ጠባይ መዋዠቅ የሚከሰቱ ከመጠን ያለፉ ሁነቶች ከሚያስከትሏቸው አሉታዊ ተፅዕኖዎች የተጠበቀ ኢኮኖሚ ማለት ሲሆን ይህም በተፅዕኖዎቹ ምክንያት የሰዎችን ደህንነትና የኢኮኖሚ እድገትን እንዲሁም የአገሪቱ የእድገት ጉዞን ጉዳት እንዳይደርስባቸው ለመጠበቅ የሚችል ነው፡፡
ስለዚህ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ግንባታ ማለት ሊመጣ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስና ሊገኙ የሚችሉ ጠቀሜታዎችን ለማሳደግ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ውጤታማ በሆነ ሁኔታ ማጣጣም ማለት ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት ላይ የሚካሄደው ድርድር የሆነው ቢሆንም የማጣጣሚያ እርምጃዎች አስፈላጊ ናቸው፡፡