የ CRGE ራዕይ እና ምሰሶዎች

የ CRGE ራዕይ እና ምሰሶዎች

የ CRGE (የአየር ንብረት መቋቋም አረንጓዴ አረንጓዴ) ራዕይ አገሪቱን በ 2025 በአየር ንብረት መቋቋም በሚችል አረንጓዴ ኢኮኖሚ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ማሰለፍ ነው፡፡

ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ቀዳሚ በመሆን በ2017 ዓ.ም መካከለኛ ገቢ ከአላቸው አገሮች ተርታ ማሰለፍ፡፡ በመሆኑም የተመረጡ የዕድገት ዘርፎች ሲከወኑ የሙቀት አማቂ ጋዞች ዓመታዊ ልቀት ከ150 ሚልዮን ሜትሪክ ቶን (1,500 ሚልዮን ኵንታል) የካርቦን ዳዮክሳይድ መጠን ሳያልፍ ወይም ዜሮ ካርበን ኢሚሽን ማድረስ ፣ ማለትም በተለመደው መንገድ ቢኬድ ኖሮ በ2022 ዓ.ምይለቀቅ ከነበረው በ250 ሚልዮን ሜትሪክ ቶን (2,500 ሚልዮን ኵንታል) የካርቦን ዳዮክሳይድ መጠን ያነሰ ሆኖ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ ያቀደችውን የኢኮኖሚ ዕድገት ልታመጣ ያስችላታል፡፡ ይህ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕቅድ በአራት /4/ ዋናዋና ምሰሶዎች የተደገፈ ነው፡፡

1. ግብርና፣ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት እየተቀነሰ እያለም የምግብ አቅርቦትን ለማረጋገጥና የገበሬውን ገቢ ለማሳደግ የሰብሎችንና የቤት እንስሳትን ምርታማነት ማሳደግ

2. የደን ​​ልማት፣ ካርቦንን ከከባቢ አየር ማግለልን ጨምሮ የሚያበረክቱዋቸው ሥርዓተ ምሕድራዊ አገልግሎቶች እንዲበራከቱ ለማድረግ ደኖች እንዲያገግሙና እንዲጠበቁ ማድረግ

3. ኃይል፣ ከታዳሽ የኃይል ምንጮች የኤሌክትሪክ ኃይልን ማመንጨቱን ማስፋፋት

4. በመጓጓዣ፣ በኢንዱስትሪና በመኖርያና በመሥርያ ቤት ሕንፃዎች ኃይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት የኃይል ብክነትን ማስቀረት፡፡

Related Posts

አካባቢ የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚወክለው የእንግሊዘኛ ቃል “ኢንቫይሮመንት” ፍቺው ኢንቫይሮነር (Environner)ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን ያጠቃለለ ማለት ነው፡፡ ይህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ

ተጨማሪ እወቅ

State of Environment in Amhara Region in 2022

State of Environment in Amhara Region

ተጨማሪ እወቅ
What are climate change adaptation activities?

What are climate change adaptation activities?

Different activities can be implemented as measures of adaptation for climate change. So far there are some 18 key actions, which are known as The

ተጨማሪ እወቅ

GHG Emission

GHG Emission_Final – 2016 (1)

ተጨማሪ እወቅ

Related Videos

3 years ago

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *