የተፈጥሮ ደን ጥበቃና አስተዳደር

የተፈጥሮ ደኖች ጥበቃና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነቶች

  • በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን ከፍተኛ የመንግስት ደኖች በመጠበቅና በማልማት ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲውሉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
  • የደን ልማት ምርምሮችን ያስተባብራል ያበረታታል እንደአስፈላጊነቱ ራሱ ያካሄዳል፤
  • የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ህጎችን በክልሉ ውስጥ ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስፈልጉትን መመሪያዎች ያወጣል፣ ተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
  • የክልሉ የደን ይዞታ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ አግባብ ላላቸው አካላት ስልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
  • በክልሉ ውስጥ የተካሄደውን የደን ሃብት ውጤቶች ዝውውር ይከታተላል ይቆጣጠራል፤
  • ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን ከፍተኛ የመንግስት ደኖችን፣ ፕሮጀክትና ሌሎች ጥብቅ ሥፍራዎችን ያጠናል፡፡
  • ትኩረት የተሰጣቸው የመንግስት፣የማህበረሰብና የማህበራት ደኖች የአያያዝና አጠቃቀም እቅድ ያዘጋጃል፤
  • በክልሉ ውስጥ ያሉትን ደኖች በባለቤነት ይዞታና ከሚሰጡት ጠቀሜታ አንጻር የሚለይበት መረጃ ሰባስቦ ያደራጃል፡፡
  • በክልሉ ውስጥ ያሉትን የመንግስትና የግል ደኖችን ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ እና አኮሎጂያዊ ጠቀሜታ ግምት ውስጥ ያስገባ ጥናት ያጠናል፤
  • የደን ዘርፉ ከሀገር ውስጥ ገበያ እና ከኢንዱስትሪ ጋር በማስተሳሰር እንዲሁም ወደ ውጭ የሚላኩ የደን ምርቶችን የምርት ጥራት በማስጠበቅ ለአጠቃላይ ኢኮኖሚ (GDP) እድገት አስተዋጽኦ እንዲኖረው ይሰራል፤
  • የክልሉን የደን ሀብት በማልማት በዘላቂነት በመጠበቅና በመንከባከብ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል ያበረታታል፤