የደን ​​ልማት እና ጥበቃ

የደን ​​ልማት እና ጥበቃ

የደን ዘርፍ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቋቋም ትልቅ ሚና የሚጫወት በመሆኑና በሀገራችን በከፍተኛ ደረጃ በደን መመናመን ምክንያት እየተከሰተ ያለውን አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመግታት ዘላቂ የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ከዚህ አንፃር የአካባቢ ፣ ደንና ​​ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን የተፈጥሮ ደኖች ጥበቃና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የሚከተሉት ዋና ዋና ኃላፊነቶች አሉት፡፡

በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን ከፍተኛ የመንግስት ደኖች በመጠበቅና በማልማት ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲውሉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤

  • በክልሉ በ5 ዞኖች በ21 ወረዳዎች ከ92,000 ሄ/ር በላይ ስፋት ያላቸው 18 የመንግስት ጥብቅ ደኖችን 4,229,280 ብር በጀት በመመደብ 330 የደን ዘበኞች ተቀጥረው ደኖች እንዲጠበቁና እንዲለሙ እያደረገ ነው፡፡

የደን ልማት ምርምሮችን ያስተባብራል ያበረታታል እንደአስፈላጊነቱ ራሱ ያካሄዳል፤

  • በአካባቢ እና ደን ምርምር ኢንስቲትዩት የሚካሄዱ ምርምሮችን አብሮ ይደግፋል ያስተባብራል፤

የክልሉ የደን ይዞታ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ አግባብ ላላቸው አካላት ስልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤

ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዋና ዋና የመንግስት ደኖችን ፣ ፕሮጀክቶችን እና ሌሎች በክልሉ የተጠበቁ ቦታዎችን በመለየት ፣ በመመዝገብና በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡

ትኩረት የተሰጣቸው የመንግስት፣የማህበረሰብና የማህበራት ደኖች የአያያዝና አጠቃቀም እቅድ ያዘጋጃል፤

Related Posts

አካባቢ የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚወክለው የእንግሊዘኛ ቃል “ኢንቫይሮመንት” ፍቺው ኢንቫይሮነር (Environner)ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን ያጠቃለለ ማለት ነው፡፡ ይህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ

ተጨማሪ እወቅ
ደንቦችን እና መመሪያዎችን ማውጣት

ደንቦችን እና መመሪያዎችን ማውጣት

የደን ​​ዘርፍ የክልሉን እና የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲያበረክት የሚፈለግ ከሆነ የደን ልማት ፣ ጥበቃ እና አጠቃቀም በአግባቡ እና በዝርዝር መመሪያዎችን እና ደንቦችን በመጠቀም መተዳደር አለበት፡፡

ተጨማሪ እወቅ
የደን ​​ምርቶች አጠቃቀም እና ቁጥጥር

የደን ​​ምርቶች አጠቃቀም እና ቁጥጥር

በክልሉ ውስጥ የተካሄደውን የደን ሃብት ውጤቶች ዝውውር ይከታተላል ይቆጣጠራል፤ በክልሉ ውስጥ ያሉትን ደኖች በባለቤነት ይዞታና ከሚሰጡት ጠቀሜታ አንጻር የሚለይበት መረጃ ሰባስቦ ያደራጃል፡ በክልሉ ውስጥ ያሉትን

ተጨማሪ እወቅ

Forest Regulation 544- 2024

Forest Regulation 544_2024 544_2016 EC 2

ተጨማሪ እወቅ

Related Videos

3 years ago

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *