የ CRGE (የአየር ንብረት መቋቋም አረንጓዴ አረንጓዴ) ራዕይ አገሪቱን በ 2025 በአየር ንብረት መቋቋም በሚችል አረንጓዴ ኢኮኖሚ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ማሰለፍ ነው፡፡
ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ቀዳሚ በመሆን በ2017 ዓ.ም መካከለኛ ገቢ ከአላቸው አገሮች ተርታ ማሰለፍ፡፡ በመሆኑም የተመረጡ የዕድገት ዘርፎች ሲከወኑ የሙቀት አማቂ ጋዞች ዓመታዊ ልቀት ከ150 ሚልዮን ሜትሪክ ቶን (1,500 ሚልዮን ኵንታል) የካርቦን ዳዮክሳይድ መጠን ሳያልፍ ወይም ዜሮ ካርበን ኢሚሽን ማድረስ ፣ ማለትም በተለመደው መንገድ ቢኬድ ኖሮ በ2022 ዓ.ምይለቀቅ ከነበረው በ250 ሚልዮን ሜትሪክ ቶን (2,500 ሚልዮን ኵንታል) የካርቦን ዳዮክሳይድ መጠን ያነሰ ሆኖ እንዳለ፣ ኢትዮጵያ ያቀደችውን የኢኮኖሚ ዕድገት ልታመጣ ያስችላታል፡፡ ይህ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕቅድ በአራት /4/ ዋናዋና ምሰሶዎች የተደገፈ ነው፡፡
1. ግብርና፣ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀት እየተቀነሰ እያለም የምግብ አቅርቦትን ለማረጋገጥና የገበሬውን ገቢ ለማሳደግ የሰብሎችንና የቤት እንስሳትን ምርታማነት ማሳደግ
2. የደን ልማት፣ ካርቦንን ከከባቢ አየር ማግለልን ጨምሮ የሚያበረክቱዋቸው ሥርዓተ ምሕድራዊ አገልግሎቶች እንዲበራከቱ ለማድረግ ደኖች እንዲያገግሙና እንዲጠበቁ ማድረግ
3. ኃይል፣ ከታዳሽ የኃይል ምንጮች የኤሌክትሪክ ኃይልን ማመንጨቱን ማስፋፋት
4. በመጓጓዣ፣ በኢንዱስትሪና በመኖርያና በመሥርያ ቤት ሕንፃዎች ኃይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት የኃይል ብክነትን ማስቀረት፡፡