የደን ዘርፍ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቋቋም ትልቅ ሚና የሚጫወት በመሆኑና በሀገራችን በከፍተኛ ደረጃ በደን መመናመን ምክንያት እየተከሰተ ያለውን አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመግታት ዘላቂ የደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ከዚህ አንፃር የአካባቢ ፣ ደንና ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን የተፈጥሮ ደኖች ጥበቃና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የሚከተሉት ዋና ዋና ኃላፊነቶች አሉት፡፡
በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን ከፍተኛ የመንግስት ደኖች በመጠበቅና በማልማት ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲውሉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
- በክልሉ በ5 ዞኖች በ21 ወረዳዎች ከ92,000 ሄ/ር በላይ ስፋት ያላቸው 18 የመንግስት ጥብቅ ደኖችን 4,229,280 ብር በጀት በመመደብ 330 የደን ዘበኞች ተቀጥረው ደኖች እንዲጠበቁና እንዲለሙ እያደረገ ነው፡፡
የደን ልማት ምርምሮችን ያስተባብራል ያበረታታል እንደአስፈላጊነቱ ራሱ ያካሄዳል፤
- በአካባቢ እና ደን ምርምር ኢንስቲትዩት የሚካሄዱ ምርምሮችን አብሮ ይደግፋል ያስተባብራል፤
የክልሉ የደን ይዞታ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ አግባብ ላላቸው አካላት ስልጠናና ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዋና ዋና የመንግስት ደኖችን ፣ ፕሮጀክቶችን እና ሌሎች በክልሉ የተጠበቁ ቦታዎችን በመለየት ፣ በመመዝገብና በማስተዳደር ላይ ይገኛል፡፡
ትኩረት የተሰጣቸው የመንግስት፣የማህበረሰብና የማህበራት ደኖች የአያያዝና አጠቃቀም እቅድ ያዘጋጃል፤