ደንቦችን እና መመሪያዎችን ማውጣት

ደንቦችን እና መመሪያዎችን ማውጣት

የደን ​​ዘርፍ የክልሉን እና የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ልማት እንዲያበረክት የሚፈለግ ከሆነ የደን ልማት ፣ ጥበቃ እና አጠቃቀም በአግባቡ እና በዝርዝር መመሪያዎችን እና ደንቦችን በመጠቀም መተዳደር አለበት፡፡ ከዚህ አንጻር በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአካባቢ ፣ ደንና ​​ዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ለባለስልጣኑ ማቋቋሚያ ወጣው አዋጅ ላይ (አዋጅ ቁጥር 232/2015) እንደተገለጸው ለክልሉ ዘላቂ የደን ልማት ፣ ጥበቃና አጠቃቀም መመሪያዎችን የማውጣት ስልጣንና ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

ስለሆነም የአደዱጥልባ የተፈጥሮ ደኖች ጥበቃና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የሚከተሉትን ዋና ዋና ኃላፊነቶች አሉት፡፡

የደን ልማት ጥበቃና አጠቃቀም ህጎችን በክልሉ ውስጥ ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስፈልጉትን መመሪያዎች ያወጣል፣ ተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፣

በአሁኑ ወቅት የኢፌዴሪ የደን ልማት ፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1065/2010 በክልሉ የደን ልማት ፣ ጥበቃና አጠቃቀምን ተግባራዊ ለማድረግ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ በዚህ አዋጅ ላይ እንደተገለጸው የደን ልማት ፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 542/1999 በአዲሱ ተሽሯል፡፡ በተጨማሪም ከዚህ በፊት በወጣው አዋጅ መሠረት በክልል እና በፌዴራል መንግሥት የወጡ ሕጎች ፣ ደንቦችና መመሪያዎች ከአዲሱ አዋጅ ጋር የማይጣጣሙ በመሆናቸው ሊተገበሩ እንደማይችሉ ተብራርቷል፡

ይህንንም ተከትሎ የአደዱጥልባ የተፈጥሮ ደን ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት የደን ልማት ፣ ጥበቃ ፣ አጠቃቀምና ቁጥጥር ዝርዝር መመሪያ አዘጋጅቷል (መመሪያ ቁጥር 002/2010)፡፡ በክልሉ ምክር ቤት የፀደቀው መመርያው በክልሉ ለሚገኙ ዞኖች ተላልፎ ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

የክልሉን የደን ሀብት በማልማት በዘላቂነት በመጠበቅና በመንከባከብ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ይደግፋል ያበረታታል፤

Related Posts

አካባቢ የሚለውን የአማርኛ ቃል የሚወክለው የእንግሊዘኛ ቃል “ኢንቫይሮመንት” ፍቺው ኢንቫይሮነር (Environner)ከሚለው የፈረንሳይኛ ቃል የተወሰደ ሲሆን በዙሪያችን የሚገኙ ነገሮችን ያጠቃለለ ማለት ነው፡፡ ይህም በቁሳዊው ዓለም ውስጥ

ተጨማሪ እወቅ

Forest Regulation 544- 2024

Forest Regulation 544_2024 544_2016 EC 2

ተጨማሪ እወቅ
የደን ​​ልማት እና ጥበቃ

የደን ​​ልማት እና ጥበቃ

የደን ዘርፍ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቋቋም ትልቅ ሚና የሚጫወት በመሆኑና በሀገራችን በከፍተኛ ደረጃ በደን መመናመን ምክንያት እየተከሰተ ያለውን አካባቢያዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን

ተጨማሪ እወቅ
የደን ​​ምርቶች አጠቃቀም እና ቁጥጥር

የደን ​​ምርቶች አጠቃቀም እና ቁጥጥር

በክልሉ ውስጥ የተካሄደውን የደን ሃብት ውጤቶች ዝውውር ይከታተላል ይቆጣጠራል፤ በክልሉ ውስጥ ያሉትን ደኖች በባለቤነት ይዞታና ከሚሰጡት ጠቀሜታ አንጻር የሚለይበት መረጃ ሰባስቦ ያደራጃል፡ በክልሉ ውስጥ ያሉትን

ተጨማሪ እወቅ

Related Videos

3 years ago

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *