በዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ስር ከተካተቱ ተግባርና ሀላፊነቶች ዉስጥ የሚከተሉት በጥናት፣ ትምህርትና ስልጠና የሚጠቃለሉ ናቸዉ።
- ለህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ስለ ጥብቅ ስፍራዎችና ብዝሃ ህይዎት ሃብትና የዱር እንስሳት ጥበቃ፤ ልማትና ዘላቂ አጠቃቀም ወቅታዊ መረጃ ተደራሽ በማድረግ ግንዛቤውንና ተሳትፎውን ማሳደግ
- የጥብቅ ስፍራ የሰዉ ሃይል አቅም በአጭርና በረዥም ጊዜ ስልጠና ማጎልበት በመሰረተልማት ማስፋፋት፤ የብዝሃ ሕዎት፣ የቱሪዝምና ሌሎች ሃብቶችን ማጥናት፣ ክትትልና ቆጠራ ማካሄድ
- መዳረሻዎችንና መስህብ ቦታዎችን ማስተዋወቅ፤ መረጃዎችን ለሚመለከታቸዉ ተደራሽ ማድረግና አለማቀፋዊ፤ አገራዊና አካባቢያዊ ፋይዳቸዉን ማስፋትና ፍትሃዊ አገልግሎት እነዲሰጥ ማስቻልና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፡፡